ሁሉም የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ተቀራራቢ ዕውቀትና ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንደሚገባ ተገለፀ

ሁሉም የልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ተቀራራቢ ዕውቀትና ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንደሚገባ ተገለፀ፤

ግንቦት 24/2017 ዓ.ም መተከል ዞን ቡለን ወረዳ፤

የግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ባበክር ኸሊፋ ሁሉም የቀበሌ ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ተቀራራቢ ዕውቀትና ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንደሚገባ ተናገሩ፤

ግብርና መዋቅር በሁሉም ቀበሌዎች ሳይንሳዊ በሆነ ሁኔታ አርሶ አደር መደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል፤

በተጨማሪም የአካባቢውን ፀጋ በመለየትና በመጠቀም ኢኮኖሚን ማሳደግ ተናግረዋል፤

የክልሉ ግብርና ቢሮ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎችን የአቅም ግንባታና ልምድ ልውውጥ መድረኮችን ለማዘጋጀት ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግስትና ፕሮጀክቶች ድጋፍ ወጪ በማድረግ ከ 3000 በላይ ሰልጣኞችን እያሰለጠነ ይገኛል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *