በመትከል ማንሰራራት በሚል ሞቶ የ2017 ዓ/ም በክረምት የሚተገበር የአራንጓደ አሸራ መረሃ-ግብር በርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በኡራ ወረዳ ሰልጋ 20 ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።
ከሀገራችን ትልቅ የስኬት ጉዞ ሊወሰድ የሚችል በአለም አቀፍ ደረጃ በአንድኝነት ወይም በሌላ ሀገራት ተደርጎ የማይታወቅ 50ቢሊዮን ችግኝ በሀገር ደረጃ እየተተከለ ይገኛል እኛም የዚህ አንድ አካል በመሆናችን ክብር ይሰማናል ሲሉ አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገረዋል።
በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ይህ መረሃ ግብረ ከተቀረፀና ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ አንስቶ 500ሚሊዮን የሚጠጉ ችግኞች እየተተከሉ ይገኛሉ ሲሉም ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ ችግኝ ሲተክል የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥና ገበያ ላይም በማዋል ለመተዳደሪያነትም የሚያገለግልም ነው ሲሉ አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናግረዋል
በዘንድሮ አመት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከግብርና ስራ ጀመሮ በጤና:በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ስራዎች ስኬታማ ሁነናል ብልዋል
።
የአረንጓዴ አሸራ መረሃ-ግብር አካባቢ መጠበቅ ብቻ ሳይይሆን የዉሃ ና የደን ሽፋን በመጨመር ለወጣቶች ና ለሴቶች ሥራ እድል በመፍጠር ጭምር አስታዋጾ እያበረከተይገኛል ያሉት አቶ ባበከር ከሀሊፋ የክልሉ የግብርና ቢሮ አላፊ።
በመረሃ-ግብሩ ዜጎች ነፃ ጉልበታቸዉ ሳይሰስቱ ከመንግስት ጎን በመሆን የአረነረጓዴ አሻራ በማኖር የአሁኑ ትዉልድ የራሱን ድርሻ ሳይጎልበት በመጠቀም ለቀጠዩ ትዉልድ ዘለቂ ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ በየአመቱ የነፃጉልበት ታስትፎ እያበረከቱ ይገኛሉ ብልዋል፡፡
ለዘንድሮ አመት ለምታደርጉት ታሳትፎ የቤ/ጉ/ክ/መ/ ግብርና ቢሮ ከልብ የመነጨ ምስጋና ለመላ ቤ/ጉ/ክ ህዝብ ያቀርባል ሲሉ ተናገረዋል።
ቤ/ጉ/ክልል የእትዮጰያ ህደሴ ግድብ መገኛ ክልል በመሆኑ በዚ ክልል የተሰራ አፈርናዉሀ ጥበቃ ስራ ና የአራንጓዴ አሻራ መኖር ለየት ያለ ትርጉም አለው ሲሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልፀዋል።
ባለፉት አመታት ሳይቋረጥ እየተገበርናቸዉ ያለውን አረንጓዴ አሻራ መረሃ – ግብር የደን ሺፋን ከማሰደግ በሻጋር የመሬት ለምነት እንዲጨምር በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የአየር ንብረት ለዉጥ ጫናን ለመቋቋም ተችሏል ብልዋል፡፡
የደረቁ ወንዞች እንደገና መመንጨት ጀምርዋል ለመስኖ ልማት መስፋፋት በአመት ከ2 ጊዜ በለይ መሬትን በመልማት መጠቀም ጀምራናል ሲሉም ገልፀዋል ፡፡
በችግኝ ተከላ መረሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ክፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የችግኝ ተከላ መረሃ ግብረ አካሂዶዋል።



