በመንደር 40 ፤በጎልማ እና በቀሽማንዶ ቀበሌዎች የተሰሩ የኢንሼቲቭ ስራዎች ምልከታ ተደረገ ‎**********************

በመንደር 40 ፤በጎልማ እና በቀሽማንዶ ቀበሌዎች የተሰሩ የኢንሼቲቭ ስራዎች ምልከታ ተደረገ
‎**********************
‎(ባምባሲ:-ጥቅምት:28/2018)በባምባሲ ወረዳ በመ/40፤በጎልማ እና በቀሽማንዶ ቀበሌዎች ላይ የተሰሩ የኢንሼቲቭ ስራዎች ምልከታ ተደርጓል።
‎የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ የእርሻ መሬት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ፀጋይ ተሰማ በምልከታጰው ላይ ተገኝተው እንዳሉ የተሰራው የሩዝና የማሽላ ኢንሼቲቭ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሆነ ጠቅሰው በዘንድሮው የተጀመረው የሩዝ ስራ ለቀጠይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉም ድርሻን ርብርብ ይፈልጋል ብለዋል።
‎የባምባሲ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጃፋር አኑር በበኩላቸው እንዳሉ ዘንድሮ በወረዳችን የሩስ እንሼይትፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለተማሪዎች ምገባም ጨምርና ለሌሎችም በቂ እንዲሆን የተደረገ ነው ብለው ከድህነት ለመውጣት ዘርፋ ብዙ ስራዎች እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልከሪም ሙሳ በምልከታው ላይ ተገኝተው እንደለው የተሰሩ ስራዎች የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው ቀጣይ ሌሎች ወረዳዎች ላይ ተሰርተው ክልላችን ከድህንነት ማውጣት አለብን ብለዋል።
‎የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ወልዴ በበኩላቸው የተጀመሩ የእንሼይትፍ ስራዎች እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት በመውሰድ በቋራጥነት መስራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
‎እየተሰሩ ያሉ የኢንሼይቲቭ ስራዎች የሚበረታታ ሆኖ የሚታዩ ምርትን የሚያጠቁ አንዳንድ በሽታዎች ወዲያው ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ መፍትሄ ሊገኝለት ይገባል ብለው የሌማት ትሩፋቶችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለድርሻ አካላት ሀላፊነት ወስደው መስራት ይኖርባቸዋል በማለት ተወያይተዋል።
‎በጎልማ ፤በመ/ር 40 እና በቀሽማንዶ ቀበሌዎች ላይ ቀጣይ የሩዝ ኢንሼቲቭን እንደሚመረቅ ተወያይተዋል።
‎በምልከታው ላይ የባምባሲ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዮሴፍ ገለታ፤የባምባሲ ወረዳ ፖሊቲካል ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳሌ መሃመድ፤እና የባምባሲ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ሻባን ሁሴን እንዲሁም የክልል ግብርና ቢሮ ባለሙያዎችና የወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ባለሙያዎችም ተገኝተውበታል።
መረጃው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ነው ።                                                                                                                   

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *