በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ 2017/18 ምርት ዘመን 289,300 ሄ/ር መሬት በቅባት እህል ተሸፈነ፤
************************************
መስከረም 30/2018 ዓ.ም ሰዳል
የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በ2017/18 ምርት ዘመን 310,050 ሄ/ር መሬት በቅባት እህል በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 289,300 ሄ/ር መሬት መሸፈኑን ገልጸዋል፤
በተለይ በዘንድሮ ምርት ዘመን 71,518 ሄ/ር መሬት በሰሊጥ ሰብል ለመሸፈን ታቅዶ አምራች ወረዳዎች ተረጋግተው ወደ እርሻ በመግባታቸው 177,149 ሄ/ር መሬት በሰሊጥ እና 81,470 ሄ/ር በለውዝ መሸፈኑን ተናግረዋል፤
በካማሽ ዞን ሰዳል ወረዳ መስተዳደር ተወካይ አቶ ተክሌ ኦሳጂ በወረዳው 35,951 ሄ/ር መሬት ከተሸፈነው 369 ሄ/ር በሰሊጥ መሸፈኑን ተናግረዋል፤
የሰዳል ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዴማ ሌቃ 1,020 ሄ/ር መሬት በክላስተር ለማረስ ታቅዶ 1,360.5 ሄ/ር በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፤
በቀጣይ ግብርናችንን ለማዘመን መካናይዜሽን በሰፊው በመጠቀም የቅባት ሰብሎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፤
የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ተሰማ በሰዳል ወረዳ የሰሊጥና የማሽላ ክላስተር ጎብኝተዋል፤














