በቤ/ጉ/ክ/መንግስት በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በሩባላገዳ ቀበሌ «በመትከል ማንሰራራት» በሚል መሪ ቃል 2ኛው ምዕራፍ 2ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ክቡር አቶ ባበክር ኃለፋ አስጀመሩ ፡፡

በቤ/ጉ/ክ/መንግስት በአሶሳ ዞን በአቡራሞ ወረዳ በሩባላገዳ ቀበሌ «በመትከል ማንሰራራት» በሚል መሪ ቃል 2ኛው ምዕራፍ 2ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ክቡር አቶ ባበክር ኃለፋ አስጀመሩ ፡፡

(አሶሳ፣ ሀምሌ 08 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ቢሮ)

በ2017/18 ዓ.ም በክልላችን 75 ሚሊየን ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ስኬታማ ስራዎች በመስራት የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ በየደረጃው ያለው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ በማድረግ ለልጆቻችን አረንጓዴ ሀገር ማውረስ እንደሚገባ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኃሊፍ አሳስበዋል ።

ክቡር አቶ ባበክር ኃሊፍ ችግኝ መትከል ምግብ መትከል በመሆኑ የአየር ንብረት ለውጥና የተፈጥሮ ሃብት መራቆትን ለመከላከል ባለፉት የተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን በመትከል ባለፉት የተከላ መርሃ- ግብሮች የተገኙትን ተሞክሮዎች በመጠቀምና ክፍተቶችን በመለየት ዘንድሮ በሚደረገው የችግኝ ተከላ አተገባበር ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ ርብርብ የታቀደውን ማሳካት እንደሚገባ የአቡራሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባበክር ሀሚድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአቡራሞ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ በበኩላቸው በዘንድሮው አመት የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ዝግጅትና ሰፊ የስነ – አካላዊ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱን ገልፀው በቀጣይ ይህን በስነ-ህይወታዊ ለመደገፍ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ከ15 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል የቅድመ-ተከላ ዝግጅቶች በሁሉም አካባቢዎች እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *