በካማሽ ዞን ደምቤ ወረዳ በ2017/18 ምርት ዘመን 40,200 ሄ/ር መሬት በዘር ተሸፈነ፤ ******************************

መስከረም 30/2018 ዓ. ም ደምቤ፤
የደምቤ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ወንድሙ ቦቦ እንደተናገሩት በ2017/18 ምርት ዘመን 40,200 ሄ/ር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፤
በክልሉ ቆላማ ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት ድጋፍ የዶሮ መንደር በማደራጀት ለ 21 ቤተሰቦች የዶሮ ግዥ መፈጸሙን የደምቤ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብራም መንግስቱ ገልጸዋል፤
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ዘመናዊ ችግኝ ጣቢያ በመገንባት ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን እያፈላ መሆኑን ተናግረዋል፤
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በወረዳው የተጀመረው የሰሊጥ ክላስተር ለሀገር ኢኮኖሚ ግብዓት ስለሚሆን ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል፤
በተጨማሪም ከሰብል መሰብሰብ ጎን ለጎን የበጋ ስራዎች የመስኖ ልማት፣ የችግኝ ዝግጅትና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ልማት በንቅናቄው ግለት ተጠናክሮ መሰራት እንደሚገባ አሳስበዋል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *