****************
(አሶሳ፣ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 11 አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደሥራ መግባታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።
መንግስት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የተናገሩት አቶ አሻድሊ፣ የአርሶ-አደሩን ሕይወት ለመቀየር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 14 የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ታቅዶ 11 አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደሥራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግሥት የፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ጥራትና ፍጥነት ማሻሻሉን ተናግረው፤ ለአብነትም የጸንጸሃሎ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
አርሶ-አደሩ የተጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ተጠቅሞ ከክረምት እስከ በጋ በማምረት ምርታማነቱን ሊያሳድግ እንደሚገባም አቶ አሻድሊ ገልጸዋል።
#የቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል_የመንግሥት_ኮሙኒኬሽን_ጉዳዮች_ቢሮ






