በክልሉ የመሻገር ማሣያ የሆኑ የሠላም እና የልማት ሥራዎችን አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን

(ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም) “በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመሻገር ማሣያ የሆኑ የሠላም እና የልማት ሥራዎችን አጠናክረን መቀጠል ይጠበቅብናል” ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

በርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የመሻገር ቀን ምክንያት በማድረግ በፓዊ ወረዳ የዶሮ ብዜት ማዕከልን እና የበለስ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጎብኝቷል።

ልዑኩ ፓዊ ወረዳ ሲደርስ በወረዳው አመራሮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አቀባበል ተደርጎለታል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በወረዳው የሚገኘውን የፓዊ የዶሮ ብዜት ማዕከልን እና የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን በጎበኙበት ወቅት፣ የመተከል ዞን በሠላም እጦት ከቆዩ አካባቢዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመው፣ አሁን በተፈጠረው አንጻራዊ ሠላም አበረታች የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በወረዳው በተለይም ለልማት ትሩፋት አበርክቶ ያላቸው ውጤቶች መኖራቸውን የገለጹት አቶ አሻድሊ፣ በክልሉ ያሉንን አቅሞች በመጠቀም እየተከናወኑ የሚገኙ የሠላም እና የልማት ሥራዎች የመሻገር ምልክቶቻችን ናቸው ብለዋል።

የበለስ መኖ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በቀጣይ ከእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያነት ባሻገር የወተት፣ የዘይት፣ የእንስሳት ማድለብ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስረድተዋል።

መንግሥት በአርሶ-አደሩ እንዲሁም በባለሃብቶች የሚከናወኑ የግብርና ሥራዎችን ለመደገፍ ይሠራል ያሉት አቶ አሻድሊ፣ የመሻገር ማሣያ የሆኑ የሠላም እና የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ መግለጻቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

ከዘመን ዘመን በምናደርገው ሽግግር የብልጽግና ጉዞን ለማሳካት የበለጠ መትጋት እንደሚገባ አቶ አሻድሊ ተናግረዋል።

የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው በቀን 1 ሺህ ኩንታል መኖ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፣ በቀጣይ ለሌማት ትሩፋት አበርክቶ ያላቸውን ምርቶች ለማምረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል ሲል የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቦታል፤

+7

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *