በክልሉ ያለው የሚታረስ መሬት በአግባቡ ለመጠቀም የኮንትራት ፋርሚንግ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በቀጣይ ወደ ትግበራ ለመግባት መታቀዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ በበክር ኸሊፋ ገልጿል።
የግብርና ምርት ውል አምራቹ እና የግብርና ሥራዎች ባለድርሻ አካሉ በቅንጅት መስራት የሚችልበት ሥረዓት የሚዘረጋ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንት እና ምርት ግብይት ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ አበበ በበኩላቸው፤ የግብርና ምርት ውል በወጣለት አዋጅ መሠረት አምራቹ በራሱ መሬት አስመራቹ ደግሞ ባለው ቴክኖሎጂ አግባብነት ባለው የመንግስት አካል ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያድርግ ነው ብለዋል።
የግብርና ምርት ውል ተሞክሮ ለገበያ መረጋጋት ሚና እንደሚጫወት የተናገሩት አቶ ደረጀ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዘርፉን የሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎች እየተከናወነ መሆኑም ጠቁመዋል።
የምርት ዉሉ ችግር ፈቺ በመሆኑ ለአምራቾች ግብዓት በማቅረብ፣አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና የብድር አገልግሎቶችን በማግኘት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።
