ክልሉ ከባህር ወለል በላይ ያለው ከፍታ ከ580 – 2730 ሜትር ይደርሳል፡፡ የክልሉ ከፍተኛ ቦታ በዳንጉር ወረዳ የበለያ ኘላቶ ሲሆን ዝቅተኛ ቦታዎች የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ በሚወጣባቸው አከባቢ የሚገኙ ናቸው፡፡ ዋና ዋና የአየር ንብረቱም 75 በመቶ ቆላ / ከ1500 ሜትር በታች፣ 24 በመቶ ወይና ደጋ / ከ1500 -2300 ሜትር/ እና 1 በመቶ ደጋ/ ከ2300 ሜትር በላይ /ሲሆን አማካይ የሙቀትና የዝናብ መጠን በቅደም ተከተል ከ17ºc? – 29 ºc? እና ከ860 – 1600 ሚ.ሜ የሚደርስ ሆኖ የዝናብ ስርጭቱ ከአምስት እስከ ስድስ ወራት ያህል ይቆያል፡፡

በክልሉ ከሚመረቱት ሰብሎች መካከል በቆሎ፣ማሽላ፣ዳጉሳ፣ሰሊጥ፣ኑግ፣ለውዝ፣አ/አተር ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ እንደ የአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ሌሎች ሰብሎች የሚመረቱ ሲሆን በማኦ-ኮም ልዩ ወረዳና በወንበራ ወረዳ የቡና ምርት በስፋት ይመረታል፡፡

ክልሉ በአባይ ወንዝ ተፋሰስና በባሮ አኮቦ ወንዝ ተፋሰስ መካከል የሚገኝ በመሆኑ የበርካታ ወንዞች ባለቤት ነው፡፡ እነዚህ ወንዞች ለአነስተኛ፣ለመካከለኛና ለከፍተኛ መስኖ ልማት የሚውሉ ናቸው፡፡ይህም የክልሉን የመስኖ ልማት 194,607 ሄ/ር የመልማት አቅም ያለዉ ሲሆን እስካሁንም ከፍተኛ የለማ 35,780 (18%)ሄ/ር መሬት ነዉ፡፡

በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንሰሳት ቆጠራ መሠረት የ2016 ዓ.ም እንደሚያሳየው 527,369 የዳልጋ ከብቶች፣153,029 በግ፣ 381,047 ፍየሎች፣ 88,119 የጋማ ከብቶች እና 1,065,747 ዶሮዎች ይገኛሉ፡፡

የክልሉ ህዝብ ብዛት በማእከላዊ ስታትስቲ ባለስልጣን 2011 ስሌት መሰረት ወንድ 571,000 ሴት 555,000 በጠቅላላዉ 1,127,000 ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ባጠቃላይ  77.09  የገጠር ነኗሪ ነዉ፡፡  የህዝብ ጥግግቱ በአማካይ 20 ሰዉ በአንድ ስኳር ኪሎ ሜትር ይሆናል ፡፡

የመሬት አጠቃቀምን በተመለከተ የታረሰ መሬት በመኸር በ2015/16 ምርት ዘመን መረጃ መሰረ 1,096,111 ሄ/ር እንደሁም በመስኖ 24,617 ሄ/ር በአጠቃላይ 867,744 ሄ/ር፤ እንዲሁም በተለየዩ የመረጃ ምንጮች መሰረት  ደን 80557 ሄር፤ ቀርቀሃ 944,759ሄ/ር፤ እንጨታማ 2,310,443ሄር፤ ቁጥቋጦ 1,259,570ሄ/ር፤ ግጦሽ 161,605 ሄ/ር፤ ረግረግ 7,250ሄር፤ ዉሃማ 15,216 ሄር እና ድንጋያማ 114,048 ሄር ይሆናል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ከመደበኛ የግብርና ስራዎች በተጨማሪ እንደሀገር ከፍተኛ ትኩረት የተደረገበት የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግርም ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተጨባጪና አበራታች ዉጤቶች የተመዘገበ ሲሆን በተለይም ደረጃዉን የጠበቀ ችግኝ ከማዘጋጀት፣የችግኝ መትከያ ቦታ ከመለየትና በተበታተነ ሳይሆን በክላስተር ችግኝ መትከል እንዲሁም ለተተከለዉ ችግኝ ባለቤት እንዲኖረዉና ተገቢዉን እንክብካቤ እንዲደረግልት ጥረት ተደርጓል፡፡

ከአረንጓዴ አሻራ በተጨማሪ እንደ ሀገር ወደ ሀገር ዉሰጥ የሚገባዉን ስንዴ ለማስቀረትና የሀገር ዉስጥ የስንዴ ፍጆታ በሀገር ዉሰጥ ምርት ተደራሽ ለማድርግ እንዲሁም ትርፍ የስንዴ ምርትን ወደ ዉጪ በመላክ የዉጪ ምንዛሬ ወደ ሀገር ለማስገባት እየተደረገ ያለዉን ጥረት በክልሉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በስንዴ ምርት የማይታወቁ የክልሉ አካባቢዎችን ጨምሮ በሁሉም አካባቢ የስንዴ ምርት በመኸርም ሆነ በመስኖ እየለማ ይገኛል፡፡

ከቅርብ  ጊዜ ወዲህ ደግሞ በሀገር ደረጃ እንዲሰራ የታያዘዉን ‹‹የሌማት ትሩፋት›› የእንስሳት ተዋጽኦ  ምርትና ምርትማነትን በማሳደግ የምግብና ስረዓት ምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፤የስራ ዕድል ፈጠራ እና የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ማሳደግ ፤የክልሉን እንስሳት ሀብት ለሀገር ያለዉን አስተዋጽኦ ማሳደግ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ  ይገኛል፡፡

በመሆኑም በባለፉት 3 ዓመታት ትግበራ ወቅት በተገኙ ውጤቶች እና ተግዳሮቶች መሰረት በማድረግ ዉጤታማ የሆኑ ስራዎችን በጥንካሬ በማስቀጠልና ክፍተት የተያባቸዉን ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ ለመተግበር የ2017 የዕቅድ አካል ተደርጓል፡፡