የዳይሬክተሩ ተግባርና ኃላፊነት
- የክልሉ የገጠር ልማት ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ስልቶች በክልሉ ውስጥ ያስፈፅማል፣ይህንኑ መሠረት አድርጎ በክልሉ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የተገናዘቡ የፖሊሲ ሃሳቦችን ያመነጫል ሲፈቀድም በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
- የግብርና ምርት ምርታማነትን ለማሳደግ ከምርምርና ከማሰልጠኛ ማዕከላት ጋር ተቃናጅቶና ተሳስሮ ይሰራል፣ ድጋፍም ይሰጣል፣
- የግብር እንቨስትመንት እንዲስፋፋ ያበረታታል፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች ሙያዊ እገዛና ክትትል ያደርጋል፣
- አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና አሰራሮችን ለተጠቃሚው ህዝብ ለማስረጽ የኤክስቴንሽን አገልግሎት በሁሉም የክልሉ አካባቢች እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ምርታማነት እንዲያድግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፣
- አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ለግብርናና ገጠር ልማት መፋጠን አስፈላጊ የሆኑ የእርሻ ሣሪያዎች፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች፣የእንስሳት መድሃኒት፣የብድር አገልግሎት እና ሌሎች የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች አገልግሎት እንዲዳረስ ጥረት ያደርጋል፣
- ቢሮው በስሩ ለሚገኙ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ፣ የመከናይዜሽንና የገጠር ቴክኖሎጂ ኤጀንሲና ማዕከላትን ለግብርናው ዘርፍ አገልግሎት ያደራጃል ፣ ያስተባብራል ፣ ይቆጣጠራል፣
- የክልሉ የተፈጥሮ ሃብት በአግባቡ እንዲጠበቅ የተዘረጋ የአሰራር ሥርዓት ተግባራዊ እንዲሆን ስልት ቀይሶ ይሰራል፣
- የነባር ብሄረሰብ ግርብርና ዘይቤ ማጥናት የተፈጥሮ ሀብቱን አባበቅና ምርታማነትን ባገናዘበ መልኩ የግብርና ዘዴ ስልት በመቀየስ ብሔረሰቦች ከዘመናዊው የግብርና ቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
- የደን ምርምርና ልማት ለማስፋፋት የሚያስችሉ የምርምር፣የግብዓት ማባዣ፣የደን ዕፅዋት ዘር ጥራት ቁጥጥር ማዕከላት እና ላቦራቶዎችን ያቋቁማል፣ያስተዳድረል፣
- የክልሉ አርሶ አደሮችን የምግብ ዋስትና የሚረጋገጥበትን መንገድ በመደገፍ ተግባራዊ ያድርጋል፣
- የአርሶ አደሩ ምርቶችን ሳያባክኑ ገበያ የሚገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል የገበያ ትስስር ሊፈጥር የሚችሉበትን ስልት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመንደፍ ተግባራዊ እዲሆኑ ያደርጋል፣
- ለአርሶ አደሩና ለግል ባለሃብቱ የሚሰጥ የዘርፍ የኤክስቴንሽን አገልግሎት ቀልጣፋና ጥራት ያለው፣ተደራሽና ውጤታማ እንደይሆን ሥርዓት ይዘረጋል፣ተግበራዊ ያደርጋል፣
- የግብርና ልማትን ለማስፋፋት የሚረዱ ሊሎች ተግባራትን ያከናውናሉ፣
- የንብረት ባለቤት ይሆናሉ፣በስሙ ውል ይዋዋላል፣ይከሳል ይከሰሳል፣
- ዓላማውን ለማስፈፀም የሚችሉ ሌሎች ተዛማች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
