የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት FSRP በ 2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃጸም እንደተመዘገበ ተገለጸ

*************************************

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት FSRP በ 2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃጸም እንደተመዘገበ ተገለጸ፤

*************************************

አሶሳ፤ ሃምሌ 9/2017 ዓ.ም፤

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት በ 2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃጸም እንደተመዘገበ ተገለጸ፤

የግብርና ቢሮ ኃላፊና የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ባበክር ኸሊፋ የስትሪንግ ኮሚቴው የቅርበት ክትትልና ድጋፍ የታቀዱ ዕቅዶች በላቀ ሁኔታ መፈጸም እንደተቻለ ገልጸዋል፤

የክልሉ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አስፋው ጃለታ በ2017 በጀት አመት ሀገራዊ የግብርና ባለድርሻ አካላት የምክክር ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፤

በተጨማሪም የአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላትን በቁሳቁስ ማደራጀት፣ የሰርቶ ማሳያዎች፣ ልምድ ልውውጦች፣ ትላልቅ ስልጠናዎች በመስጠት ተሞክሮ የተቀመረበት ጊዜ እንደነበር ገልጸዋል፤

ከሁሉም በላይ ለ 1400 አርሶ አደሮች በ 365 ሄ/ር መሬት የመስኖ እርሻ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፤

በ አንድ አመት ውስጥ ሁለት አነስተኛ መስኖ ግንባታ እና በ 18 ሚሊየን ብር ቢሮ በመገንባት ርክክብ መደረጉን አቶ አስፋው ጃለታ ተናግረዋል፤

በአጠቃላይ በ2017 ከተመደበ 120,751,015 ብር ከፌዴራል ተጨማሪ በጀት በመጠየቅ 144,868,706.71 ብር በአግባቡ መጠቀም እንደተቻለ ተገልፆል፤

የክልሉ FSRP ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ የ 2017 የሥራ አፈፃጸም በመገምገም ለ 2018

በጀት አመት 114,055,614 ብር የሥራ ዕቅድ አጸድቋል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *