
የክልሉ ግብርና ቢሮ በዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ሁለት አዲስ የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመገንባትና ሁለት ቤቶችን ከማደስ በተጨማሪ ለ100 አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች ለእያንዳቸው 10ኪ.ግራም የዳቦ ዱቄት ና 17 ካርቶን ባለ ሶስት ዘይት ማዕድ ማጋራቱንና ለ 317 የድሃ ድሃ ቤተሰብ ተማሪዎች 200 ደርዘን ባለ50 ወረቀት ደብተር፣30 ፖኬት ቢክ እስክርቢቶ እና 50 የተማሪዎች ቦርሳ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ተሰማ ተናግረዋል።
የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር ላይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በማስተባበር ባህልና እምነቱ በሚያዘውና በሚፈቅደው አቅመ ደካሞችን መርዳት፣በጎ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል፣በመደጋገፍ፣አብሮነታችንና አንድነታችን ልናጎለብት ይገባል ሲሉ አቶ ፀጋዬ ተሰማ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ በካማሺ ከተማ የአቅመ ደካማ ቤቶችን በመገንባት፣በማደስ፣ማዕድ በማጋራት እና ለድሃ ቤተሰብ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የተሰሩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች የወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚያጠናክር ተግባር ነው ሲሉ የካማሽ ከተማ ከንቲባ አቶ ጊሽላይ ደንጋሽ ገልጸዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የማዕድ ማጋራቱና የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሳካ ላደረጉ ለካማሽ ከተማ አስተዳድር አመራሮች፣ቡድን መሪዎች፣ባለሙያዎች እና ግለሰቦች የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ተሰማና ኮሚቴዎች ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
