የቤ/ጉ/ክ/መ/ ግብርና ቢሮ በአየር ንብረት አፈፃፀም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (Climate Action through Land Scape Management Program for result CALM-P4R) የተዘጋጀየ 1ኛ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የስራ አቅጣጫን በተመለከተ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዉይይት አካሄደ። (አሶሳ፣ ህዳር 10 / 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ቢሮ)

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ግብርና ቢሮ በአየር ንብረት አፈፃፀም የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (Climate Action through Land Scape Management Program for result CALM-P4R) የተዘጋጀየ 1ኛ የሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ የስራ አቅጣጫን በተመለከተ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዉይይት አካሄደ።
(አሶሳ፣ ህዳር 10 / 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ቢሮ)
ካልም ፕሮግራም የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሻሻል፣ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማትን በማሳካት፣ የአፈር ለምነትን በማሻሻልና የውኃ ሀብት አቅምን በማጎልበት የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምቹ ተፈጥሮን በመገንባት የጎላ ሚና ገምብቷል ሲሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አብዱልከሩም ሙሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል ።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተከናወኑ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ በማህበራት መመዝገቡንና በተያዘውበጀት ዓመት በተሻለ መጠናከር እንዳለበት አቶ አብዱልከሪም ሙሳ ገልፀዋል፡፡
የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALM P4R) የ2017/18 የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ሰነዶች በESMS Specialist በአቶ ምግባሩ መርጊያው ߹ በGIS Specialist በአቶ ሙለታ ብዙ እና በወረዳ አስተባባሪዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የክልሉ የካልም ፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አያሌው መልኬ በወረዳ ደረጃ በዘላቂ የመሬት አያያዝ አየር ንብረት ለውጥ በተሰራው ስራ ተፈጥሮን በመንከባከብ ትውልድ ተሻጋሪ የአፈርና ውሀ ጥበቃ መሰራቱን ገልጸው ቀጣይ መሻሻል ያለባቸውን ክፍተቶች በማረም የተሻለ ስራ ለመስራት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በካልም ፕሮግራም የተደራጁ ማህበራት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ በመሆኑ የፕሮግራሙን ዓላማ ለማሳካት መሰረት ባደረገ መልኩ በንዑስ ተፋሰስ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብት በዘላቂነት ማልማት እና መጠበቅ ያስፈልጋል ሲሉ አቶ አያሌው መልኬ ተናግረዋል ።
የተነሱ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም በጀትን ለታለመለት ዓላም እንዲውል በቅንጅትና በትኩረት እንደሚሰሩ የውይይቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *