የቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የዘላቂ መሬት አያያዝ /RLLP-2/ ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተጠናቀቀ፡፡
(አሶሳ፣ ሀምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ቢሮ)
RLLP-2 ፕሮጀክት የአካባቢውን ማህበረሰብ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ከተረጅናት ነፃ በማውጣት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ባበክር ኃሊፍ በመክፈቻ ንግግራቸቸው ተናግረዋል ፡፡
ፕሮጀክቱ በበጀት አመቱ ለሌሌች ክልሎ ሞዴል የሚሆኑ በአይን የመሚታዩ የማህበረሰብ አቀፍ የተቀናጀ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ንዑስ ተፋሰሶችን߹ የማህበረሰቡን የዘመናት ጥያቄ የነበሩትን የንፁህ መጠጥ ውሃ ߹ የመንገድ ስራ እና በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ክቡር አቶ ባበክር ኃሊፍ ገልፀዋል
ኡራ߹ዛይ እና ድባጢ ወረዳዎች የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶች በፕሮጀክት አስተባባሪዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
ፕሮጀክቱ ለምነታቸቸውን ያጡ መሬቶችን በመለየት በችግኝ ጣቢያዎች ችግኝ በማፍላትና በመትከል የተፋሰስ ስራዎችን በመስራት ለምነታቸውን በመመለስ የአካባቢው አርሶ- አደር በመኖ ልማት߹ በእቀባ እርሻ ߹ በቨርሚ ኮምፖስት በማዘጋጀት እና በኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ላይ በ2017 በጀት አመት የታለመለትን ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የፕሮቸክቱ አስተባባሪ አቶ ታደሰ ቢራቱ ገልፀዋል ፡፡
በቀጣይ በጀት አመት የሚሰሩ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ንዑስ ተፋሰሶች ከ90% በላይ መከናውን እንዳለባቸውም አቶ ታደሰ ቢራቱ ተናግረዋል ፡፡
የፕሮጀክቱ የቀጣይ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በፕሮጀክቱ ባለሙያ በአቶ ደረጃ ቸርነት ለቴክኒክ ኮሚቴዎች እና ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ለቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፡፡






