የቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ FSRP ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት ከቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር ግምገማ አካሄደ፡፡
(አሶሳ፣ ሀምሌ 07 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ቢሮ)
የክልሉ ግብርናና ቢሮ የFSRP /የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም/ የ2017 በጀት ዓመት የአርሶ አደሩ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ፕሮጀክቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና ዘመናዊ አሰራሮችን በማዘመን የአንስተኛ የመስኖ ግንባታዎችን በተያዘላቸው እቅድ መሰረት በማጠናቀቅ ህብረት ስራ ማህበራትን በተለያዩ የስራ ዘርፎች በማደራጀት ወደ ተቀናጀ ግብርና ለማስገባት ትኩረት በመስጠት በመስራታችን ትልቅ ስኬት ማከናወን ችለናል ሲሉ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አስፋው ጃለታ ተናግረዋል ፡፡
የFSRP የአርሶ – አደር ማሰልጠኛ ተቋማት ወደ ስራ ማስገባት ߹ቨርሚ ኮምፖስት እና እቀባ እርሻዎችን በማዘጋጀት ወደ ስራ በማስገባት የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ማሳካት መቻሉን አቶ አስፋው ጃለታ ገልፀዋል፡፡
የ2017 ዓመት በጀት የተከናወኑ የዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት በFSRP ፕሮጀክት እቅድ ዝግጅት ባለሙያ በአቶ ታዘበው ጉግሳ ለቴክኒክ ኮሚቴ አካላት ቀርቦ ከተገመገመ በኋላ የፕሮጀክቱ ቀጣይ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድና የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት በማድረግ በተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፡፡




