የክልሉ GCF (Green Climate Fund) ፕሮጀክት ያለፉት 6 ዓመታት ፊዚካልና ፋይናንሻል ሪፓርት ማጠቃለያ ምዕራፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተገመገመ።
(አሶሳ፣ ህዳር 05/2018ዓ.ም) የክልሉ GCF (Green Climate Fund) ፕሮጀክት ያለፉት 6 ዓመታት ፊዚካልና ፋይናንሻል ሪፓርት ማጠቃለያ ምዕራፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተገምግሟል።
በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የተመራው የፌደራል እና የክልል GCF ቴክኒክ ኮሚቴ በሸርቆሌና ኡራ ወረዳ በመጠጥ ውሃ እና መስኖ ዘርፍ ላይ በፕሮጀክቱ የተሰሩ ፊዚካል ስራዎች እና አጠቃላይ ፋይናንሻል አፈፃፀሙን ምልከታ አድርገው ተገምግሟል።
በውይይት መድረኩ በፊዚካልም ሆነ ፋይናንሻል አፈፃፀም ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና የታዩ ክፍተቶች የተመላከቱ ሲሆን በአስቸኳይ እንዲታረሙ ተገልጿል።
የፕሮጀክቱ ያለፉት 6 ዓመታት ማጠቃለያ ምዕራፍ እና ለሌላ ፕሮጀክት ቀረፃ መነሻ እንደመሆኑ የታዩ ክፍተቶች በጊዜ ታርመው ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ ማቅረብ እንደሚገባ ተመላክቶ በፕሮጀክቱ የተጀመሩ ስራዎችን ስለማይቆሙ በመንግስት በኩል ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ፣ግብርና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ውሃ ቢሮ ቴክኒካል ኮሚቴ እንዲሁም የፌደራል ገንዘብ ሚኒስቴር GCF አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል።

