1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-

      የተቋሙን የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሥራዎች በፋይናንስ ደንብና መመሪያ መሠረት እየተከናወኑ መሆናቸውን መመርመርና የኦዲት ሪፖርት ማዘጋጀት

2. የሥራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት 1 የኦዲት ተግበራትን ማከናወን፡፡

      የኦዲት ፕሮግራም ያዘጋጃል፡፡

      የፋይናንስ አጠቃቀም አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን የጠበቀ መሆኑን በፋይናንሺያል ኦዲት ያረጋገረጣል፣

      የስጋት አካባቢ የዳሰሳ ጥናት ያካሒዳል፣ በጥናቱ ውጤት መሰረት የኦዲት ፕሮግራም ያዘጋጃል፣

      መ/ቤቱ አላማውን ከግብ ለማድረስ የሚከተለው የሥራ አፈጻጸም ስልት ኢኮኖሚያዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ የክዋኔ ኦዲት ያካሒዳል፣

      በተደደሰባቸው የኦዲት ግኝቶች ላይ የኦዲት ሪፖርት በማዘጋጀት ለኃላፊው ያቀርባል፣

ውጤት 2፡- ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

      የኦዲት አስተያየት የተሰጠባቸውን ጉዳዮች ላይ ክትትል ያደርጋል፡፡

      ተግባራዊ ላልተደረጉ የእርምት እርምጃዎች ተፈጻሚ የሚሆኑበትን የመፍትሄ ሐሳብ ያቀርባል፣

      ለተቋሙ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣

      ለውጭ ኦዲተሮች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣