የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የውሃ መሳቢያ ጀኔሬተር ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ አደረገ ፡፡ *****************

የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የውሃ መሳቢያ ጀኔሬተር ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ አደረገ ፡፡
*****************
ህዳር 4/2/2018 ዓ.ም አሶሳ
የፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የውሃ መሳቢያ ጀኔሬተር ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስራት ስራ አመራር ኮሚሽን ርክክብ አድርጓል፡፡
ርክክቡን ያደረጉ በፌዴራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ የተጎጅዎች የኑሮ መሰረቶችና ማህበራዊ አገልግሎቶች ማስተባበርያ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ቤቶ ዲማ እንዳሉት በክልሉ ባለፉት አመታት ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው ወደ ነበሩበት ቀዪ ለተመለሱ ተፈናቃዮች በማህበር በማደራጀት የመስኖ እርሻ ልማት በዓመት 3 ጊዜ እንዲሰሩ እና ራሳቸውን ከተረጃነት በማላቀቅ የራሳቸውን ኑሮ እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ታስቦ 15 የውሃ መሳቢያ ጀነረተሮችን ድጋፍ መደረጉን በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል፡፡
በርክክቡ ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብዱልአዚዝ እንዳሉት ለክልሉ የተደረገውን ድጋፍ በማመስገን ጉዳት የደረሰባቸውን ተፈናቃይ አርሶአደሮችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በቀጣይ በመስኖ ሊለማ የሚችል የጓሮ አትክልቶችን ዘር በማፈላለግ ከውሃ ቢሮ የጀኔረተር ጥገና እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ በማድረግ እንደሚሰራ በመግለጽ በቀጣይም ለሴቶች፣ለህጻናትእና አረጋዊያን ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች አስፈላጊው ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚደረግ አሳስበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *