በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለሁሉም የብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፤

 በዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለሁሉም የብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፤
የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ፍቃዱ ደሳለኝ በሰዎች አያያዝና አጠቃቀም ጉድለት የተነሳ እየተመናመነና እየጠፋ የሚገኘውን ብዝሃ ህይወት የመጠበቅና የማቆየት ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል፤
የብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጉተታ ብርሃኑ የአካባቢ ስነ ምህዳር በዘላቂነት ለቀጣይ ትውልድ ባለበት ለማቆየት የብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች በእውቀት እና በስትራቴጂ መምራት እንደሚገባ ገልጸዋል፤
በተለያየ መንገድ የገባው መጤ ወራሪ አረም አርሶ አደሩ ከተወለደትን ቀበሌ እንዳይሰደድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በጋራ መስራት፣ መከታተልና መቆጣጠር እንደሚገባ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፤
የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ የብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ባለሙያዎች በተለያዩ የዳሰሳ ጥናቶች ላይ እና የቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፤
+4
All reactions:

14