በመተከል ዞን በወምበራ ወረዳ የ2016 ለ2017 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ወቅቱን በጠበቀ መልኩ የማጓጓዝና ለአርሶ አደሩ የማሠራጨት ስራ በከፍተኛ ንቅናቄ ተጀምሯል።የወምበራ ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ቀነኒ በወረዳው ገሰንገሳ ቀበሌ በመገኘት የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝና ስርጭት ስራን በጎበኙበት ወቅት እንዳሉት:-በምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭትና የማጓጓዝ ስራ በዞኑ ግብርና መምሪያና ክልል ግብርና ቢሮ በኩል ደንብና መመሪያን ተከትሎ ጨረታ በማውጣትና ግዥ በመፈፀም ወደ ወረዳ ብሎም ቀበሌ ድረስ የማጓጓዝና ለአርሶ አደሩ የማሠራጨት ስራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፅዋል።
አቶ ተሻለ አያይዘውም:-በበጀት ዓመቱ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭቱ አርሶ አደሩ ያለምንም እንግልትና ውጣ ውረድ ከሚኖርበት ቀዮና ቀበሌ ድረስ ግብዓት እንዲወስድ መደረጉ ከባለፉት ጊዜያት ለየት እንደሚያደርገው በመግለፅ ከዚህም ተግባር አርሶ አደሩ ከህገ-ወጥ ደላሎችና ያለአግባብ ወጪ ማዳን እንደተቻለ ተናግረዋል።
አርሶ አደሩ መንግስት ያመቻቸለትን ይህንን መልካም አጋጣሚና እድል በመጠቀም መንግስት በተመነው የማዳበሪያ ዋጋ ግዥ በመፈፀም ለበጀት ዓመቱ የምርት ዘመን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግም አቶ ተሻለ አሳስበዋል።
በወረዳው ግብርና ልማት ፅህፈት ቤት የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ቡድን መሪ አቶ ነገሪ ታደለ በበኩላቸው;-በወምበራ ወረዳ በያዝነው የምርት ዘመን ከ32 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አርሶ አደሩ ለማሰራጨት የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥም የእቅዱ 48 ነጥብ 5% የሚሆነው የግብዓት አቅርቦት ተጓጉዞ ወምበራ እንደደረሰ በመግለፅ በመጀመሪያ ዙር ስርጭት 1 ሺህ 5 መቶ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት እንደተቻለ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው በምርት ዘመኑ 2 ሺህ 2 መቶ 75 ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ለማሰራጨት ታቅዶ 2 መቶ 95 ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ለማቅረብና ለማሠራጨት ከአርሶ አደሩ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አቶ ነገሪ አክለው ገልፀዋል።
አሁን ላይ መንግስት ያለምንም የትራንስፖርትና ወጪ ቀበሌያቸው ድረስ ማዳበሪያ ስላቀረበላቸው በእጅጉ መደሰታቸውንና ለተደረገላቸዉ ትብብርም ምስጋናቸዉ የላቀ መሆኑን ያነጋገርናቸው የወረዳው አርሶ አደሮች ተናግረዋል።
በ2016/2017 በጀት ዓመት 95 ሺህ 9 መቶ 45 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈንና የማሳ ፅዳት ለማድረግ ታቅዶ 6 ሺህ 9 መቶ 21 ሄክታር መሬት ማሳ ለመኸር እርሻ ፅዱ እንደሆነና ከዚህም ውስጥም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ 3 ሺህ 7 መቶ 58 ሄክታር መሬት በላይ በዘር መሸፈኑን ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።





+5
All reactions:
Dereje De Negn, Guteta Birhanu and 51 others




All reactions:
37
