በክልሉ እየተሻሻለ የመጣው የመስኖ እርሻ አጠቃቀም ባህል አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ እያገዘ ነው❞

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አርሶ አደር የመስኖ አጠቃቀም ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ እያገዘ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በአሶሳ ዞን ዑራ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የበጋ መስኖ እና የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን ተዘዋውረሮ ጎብኝቷል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በወረዳው በ205 ሄክታር ማሳ ላይ በመስኖ እየለማ የሚገኘውን የበቆሎ ማሳ እና በወረዳው እየተከናወኑ የሚገኘውን የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
አቶ አሻድሊ ሀሰን በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የመስኖ ስራዎች በአርሶ አደሩ ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጦች ማሳየት ጀምረዋል።
የክልሉ አርሶ አደር የመስኖ አጠቃቀም ባህሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመው፣ ይህም አርሶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ እያገዘ ነው ብለዋል
ለዓመታት ያለጥቅም ሲፈሱ የነበሩ ወንዞችን በመጥለፍ መስኖን በማልማት የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ አሻድሊ ገልፀዋል።
መንግስት በክልሉ መለስተኛ የመስኖ ግድቦችን በመገንባት በአርሶ አደሩ ዘንድ የቤተሰብ ብልፅግናን በማረጋገጥ ከዝናብ ጥገኝነት እንዲላቀቁ እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።
አርሶ አደሩ የኩታ ገጠም የአስተራረስ ዜዴዎችን በማዘመን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት መሠጠቱንም አመልክተዋል።
በጉብኝቱም ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር፣ እንዲሁም ሌሎች የክልል እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
+3
All reactions:

Taddesse Biratu, Teshome Getachew and 43 others