የአካባቢ ስነምህዳርን ያሻሻለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች የአካባቢ ስነምህዳርን በማሻሻልና ለምግብነትም በመዋል ጭምር ውጤት ማሳየት ጀምረዋል።

በክልሉ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ስድስት ዓመታት በተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብሮች ከ250 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

እነዚህ ችግኞች ታዲያ አሁን ላይ የአካባቢን ስነምህዳር በማሻሻልና ለመግብነት በመዋል ጭምር አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡

በክልሉ የሚታወቀውን የማንጎ ችግኝ ጨምሮ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ብርቱካን ሙዝና ቡናን የመሳሰሉት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ፍሬ በማፍራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ክልሉ በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርኃ ግብርም 75 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እስካሁን ድረስም ከ60 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መሆናቸውን ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

በክልሉ የዘንድሮውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከቀናት በፊት በርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

በጀማል አህመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *