‎”የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ 2.5 ሚሊየን ብር የሚገመት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ እንደሚሠራ ገለጸ፤ ……አቶ ባበክር ኸሊፋ

**************************************

ሀምሌ 3/2017 ዓ.ም አሶሳ፤

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ 2.5 ሚሊየን ብር የሚገመት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሥራ እንደሚሠራ ገለጸ፤ ……አቶ ባበክር ኸሊፋ

የክልሉ ግብርና ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በተካሄደው ውይይት በካማሽ ወረዳ አቅመ ደካማ ለሆኑ ሁለት አዲስ መኖሪያ ቤት እና ሁለት መኖሪያ ቤት እድሳት፣ 200 ደርዘን መማሪያ ደብተር፣ 30 ካርቶን እስክርቢቶና 50 የተማሪ ደብተር መያዣ ቦርሶ እንዲሁም 100 አቅመ ደካማ ሰዎች ማዕድ ለማጋራት ወስኗል፤

የክልሉ መንግስት ለክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎች 222,272,500 ብር በጀት መያዙ ይታወቃል፤

በመጨረሻም የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ የቢሮ፣ የማዕከልና የፕሮጀክት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎች በንቃት እንዲሳተፋ ጥሪ አቅርበዋል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *