በፌዴራል ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮምቴ በግብርና ቢሮ በኩል የምርት ዘመኑን የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት አፈፃጸም ሪፖርት ገመገመ።

  ሐምሌ  7/2017 ዓ/ም 
        አሶሳ

የ2016/17 እና 2017/18 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭት የተመለከተ የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በቀለ ባቀረቡት ሪፖርት የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በየጊዜው የምያቀርባቸው ቴክኖሎጂዎች ምርት ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል ።

የ2017/18 ምርት ዘመን የመኸርና የመስኖ እርሻን ጨምሮ የተሰራጨ NPS 74,224 ኩ/ል ሲሆን ዩሪያ 51,354 ኩ/ል በድምሩ 125,578 ኩ/ል መሰራጨቱን አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።

የግብዓት ሰንሰለቱን በማስተካከል በዘርፉ የነበረውን የማጭበርበርና ስርቆት ሙሎ በሙሎ መቀረፍ መቻሉን የግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ባበክር ሃሊፋ ለቋሚ ኮሚቴዎች ሰፍ ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የግብዓት ስርጭት በመከታተል በዘርፉ የነበሩ የአርሶ አደርና ባለሀብቶች መጉላላት እንደሚቀረፍ አሳስቧል ።

በመጨረሻም በቀረበው ሪፖርትና ከቢሮ በተሰጠው አስተያየት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ግብርና ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ክልሉ የተከተለው አቅጣጫ ለሌሎች ክልሎች ጥሩ ተሞክሮ መሆን እንደምችል በመግለጽ ቢሮውን አመስግነዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *