
መስከረም 4/2018 ዓ.ም አሶሳ፤
የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በአሶሳ ዞን ኡንዱሉ ወረዳ አዶናስ እርሻ ልማት ድርጅት 60 ሄ/ር የሩዝ ማሳ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገለፁ፤
አዶናስ እርሻ ልማት ድርጅት በክላስተር 24 ሄ/ር ዘር ብዜት በቆሎ፣ 71 ሄ/ር አኩሪ አተር፣ 60 ሄ/ር ሩዝ፣ 15 ሄ/ር ዳሞትና 14 ሄ/ር ሊሞ የበቆሎ ዘርና 4 ሄ/ር በርበሬ እየለማ መሆኑን ገልጸዋል፤
አቶ ባበክር ኸሊፋ ባለሃብቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና ዝርያዎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ የማስተዋወቅ ሰራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፤
