የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በካማሽ ዞን ዛይ ወረዳ ወቅታዊ የግብርና ሥራዎችን ጎበኙ፤ ************************************

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በካማሽ ዞን ዛይ ወረዳ ወቅታዊ የግብርና ሥራዎችን ጎበኙ፤
************************************
መስከረም 28/2018 ዓ. ም ካማሽ፤
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በካማሽ ዞን ዛይ ወረዳ ወቅታዊ የግብርና ሥራዎችን ጎበኙ፤
የካማሽ ዞን ግብርና መምሪያ አቶ ፈረንጂ ቦጂ በ2017/18 ምርት ዘመን 330,620 ሄ/ር ማሣ በዘር ለመሸፈን አቅደው 340,326 ሄ/ር በተለያዪ ሰብሎች መሸፈኑን ገልጸዋል፤
በተጨማሪም 23,735 ሄ/ር በክላስተር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 68,555.5 ሄ/ር መፈጸም መቻሉን ተናግረዋል፤
በካማሽ ዞን ዛይ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አየለ በግዱ በ2017/18 ምርት ዘመን ህዝባችን ባገኘው ሠላምና መረጋጋት 62,848 ሄ/ር ማሣ ለማልማት ታቅዶ 85,790 ሄ/ር መሬት መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል፤
የዛይ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ገነቴ መንግስት በሰጠን የትኩረት አቅጣጫ 1990 ሄ/ር ማሣ በክላስተር ለመዝራት አቅደን 5790 ሄ/ር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል፤
በተለይ በማሽላ፣ በቆሎና የቅባት እህሎችን ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ማሾ ዘር አርሶ አደሩ በመደራጀት በክላስተር ማልማት እየተለመድ መምጣቱን ገልጸዋል፤
በመጨረሻም የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ በራስ አቅም የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ኢኮኖሚን ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፤
በተለይ በመኸር የተጀመረው የክላስተር እርሻ በመስኖ፣ በአፈርና ውኃ ጥበቃና በችግኝ ተከላ ሁሉ በክላስተር መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፤
በቀጣይ የበጋ ወራት ከወዲሁ ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ማፍላትና የሚተከልበትን ቦታ ማዘጋጀትና መለየት እንደሚገባ ተናግረዋል፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *