‎የኩርሙክ ወረዳ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በኩርሙክ ወረዳ የተረጂነት ቅነሳ ስራ ለማከናወን በ8 ሄክታር ማሳ ላይ ያረፈ ማሽላና የሌማት ቱሩፋት ስራ የመስክ ምልከታ አደረጉ

‎የኩርሙክ ወረዳ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በኩርሙክ ወረዳ የተረጂነት ቅነሳ ስራ ለማከናወን በ8 ሄክታር ማሳ ላይ ያረፈ ማሽላና የሌማት ቱሩፋት ስራ የመስክ ምልከታ አደረጉ
‎(ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም)
የኩርሙክ ወረዳ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በኩርሙክ ወረዳ የተረጂነት ቅነሳ ስራ ለማከናወን በ8 ሄክታር ማሳ ላይ ያረፈ ማሽላና የሌማት ቱሩፋት ስራ የመስክ ምልከታ አደረጉ።
‎የኩርሙክ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዩሱፍ ኡዳ ቋሚ ኮሚቴው በወረዳ ደረጃ የተከናወኑ የሌማት ቱሩፋት መስክ ምልከታ በማድረግ የቀጣይ ተኩረት አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ ነው ብለዋል።
‎የወረዳው ግብር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልከሪም ዮሚድ በበኩላቸው መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ‎በወረዳው የምርትና ምርታማነት ስራ እና የሌማት ቱርፋት ስራ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግሯል።
‎አቶ አብዱልከሪም በወረዳ ደረጃ በ8 ሄክታር ማሳ በዘር የተሸፈነ ማሽላ፣የእንሰሳት እርባታ ፍየልና ቤግ በዛሬው ዕለት ምልከታ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በየ3ወሩ 500 ዶሮ ለማስገባት እና የንብ ቆፎ ቦታዎች ዝግጁ መደረጋቸውን ገልጿል።
‎የኩርሙክ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከማል መሀመድ በሌማት ቱሩፋት የተከናወኑ ስራዎች እጅግ አበረታች እና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግሯል።
‎አስተዳዳሪው አክለው አሁንም ቀሪ ስራዎችን በመስራት እና በሟሟላት ወረዳውን በሌማት ቱሩፋት ሞዴል በማድረግ ለጉብኝት ምቹ እናደርጋለን ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *