በመተከል ዞን በተያዘው የመርኸር እርሻ 19 ሚሊዮን 404 ሺ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ።

በመተከል ዞን በተያዘው የመርኸር እርሻ 19 ሚሊዮን 404 ሺ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ። (ህዳር 3/2018) መምሪያው በዞኑ ውስጥ ከተለያዩ ሰብሎች 19 ሚሊዮን 404ሺ ኩንታል ምርት ለማግኘት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል። የመተከል ዞን ግብርና መምሪያ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር በወረዳው በተያዘው የመኸር እርሻ በፓዊ ምርምር ማዕከል አማካኝነት እየለሙ የሚገኙ የሩዝና የአኩሪ አተር ሰብሎች ላይ የአርሶ አደሮች የመስልክ ምልከታ በዓል አካሂዷል። የመተከል ዞን ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓባይ፤ በተያዘው የመኸር እርሻ 512ሺ 523 ሄክታር መሬት ላይ በተለያዩ ሰብሎች በዘር በመሸፈን 19 ሚሊዮን 404 ሺ ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እየተደረገ ባለው ርብርብ ከ43ሺ ሄክታር መሬት በላይ በተለያዩ ሰብሎች በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ሃላፊው አክለው ገልጸዋል። የፓዊ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደስታ አበበ፤ማዕከሉ በመተከል እና አዊ ዞኖች ከ3 መቶ ሄክታር መሬት በላይ በሶስት የሩዝ ሰብል ዝርያዎች ላይ የማስታዋወቅ ስራ በመስራት ረገድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ማዕከሉ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማሳደግ እንደ ሀገር በአኩሪ አተር፣ሩዝና ሰሊጥ ሰብሎች ላይ የምርምር ቴክኖሎጂዎችን ማውጣት፣የመነሻ ቴክኖሎጂ ማባዘትና የተመረጡትን ደግሞ በማስተዋወቅ ረገድ ዓላማ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የዳንጉር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ደስታየሁ አብሾክ በበኩላቸው፤በወረዳው ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑ ሰብሎችን በዘር ብዜት በማባዛትና ወደ አርሶ አደሩ በማሰራጨት በኩል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል። በዞኑ ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የዘርፉ የስራ ሃላፊዎች፣ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች በዳንጉር ወረዳ በኩታ ገጠም እየለሙ በሚገኙ የሩዝ፣የአኩሪ አተርና የበቆሎ ሰብሎች ላይ እየተከናወነ ያለውን የዘር ብዜት ልማት ተዘዋውረው ምልከታ ማድረጋቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *