የሩዝ ሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የምርምር ስራ እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ተቋም የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።

የሩዝ ሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የምርምር ስራ እየተከናወነ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ተቋም የፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
ማእከሉ በሄክታር እስከ 58 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችሉ የሩዝ ዝሪያ በምርምር ማግኘቱን አስታውቋል።
በአኩሪ አተር ሰብል ምርትና ምርታማነት ምርምር ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቀው የፓዌ ግብርና ምርምር ማእከል አሁን ደግሞ የሩዝ ምርታማነትን ለማሳደግ በተለያዩ የሩዝ ዝሪያዎች ላይ ምርምር እያደረገ ይገኛል።
በፓዌ ግብርና ምርምር ማዕከል የሩዝ ሰብል ተመራማሪና የማእከሉ ዳይሬክተር አቶ ደስታ አበበ እንዳሉት ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በተለይ መተከል ዞን ለሩዝ ሰብል ተስማሚ የሆነ ስነ ምህዳር ያለው ቢሆንም አርሶ አደሩ ይህንን ተጠቅሞ በሩዝ ሰብል ልማት ዘርፍ እንዲሰማራ የተሰሩ ስራዎች አነስተኛ ናቸው ብለዋል።
ማእከሉ ከባለፉት 5 ዓመታት ጀምሮ የሩዝ ሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና አርሶ አደሩ በዘርፉ እንዲሰማራ ለማስቻል እያካሄደ ያለው የምርምር ስራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን አቶ ደስታ ተናግረዋል።
ማእከሉ ከ12 በላይ በሚሆኑ የሩዝ ዝሪያዎች ላይ ባካሄደው የምርምር ስራ በሄክታር እስከ 58 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችል ኢካፋሲ የተባለ የሩዝ ዝሪያ ማግኘቱን አቶ ደስታ ተናግረዋል።
በቀጣይ ማእከሉ የምርምር ውጤቶችን ወደ አርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም ተመራማሪው አስታውቋል።
በማእከሉ የቴክኖሎጂ ብዜትና የዘር ተመራማሪ አቶ በውቀት ጌታቸው በበኩላቸው በማዕከሉ በኩል በምርምር ውጤታማ ሆነው የተገኙ የሩዝ ዝሪዎችን ለአርሶ አደሩና በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ተደራሽ ለማድረግ በ8 ሄክታር ላይ ለዘር ብዜት የሚሆን የሩዝ ሰብል ማልማት መቻሉን ተናግረዋል።
ማእከሉ መነሻ ዘር ማቅረብ እንጂ የዘር ብዜት ስራ አይሰራም ያሉት አቶ በውቀት ቀጣይ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ዘር አባዢዎች በዘርፉ እንዲሰማሩ ጠይቋል።
@BGM

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *