የክልሉ ግብርና ቢሮ በበኩሉ አኩልቶ የተባለ የስንዴ ዘር በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እያሰራጨ መሆኑን ገልጿል፡፡
የበጋ መስኖ ስንዴ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በመላ ሀገሪቱ በስፋት እየተመረተ የሚገኝ እና አዋጭ እየሆነ የመጣ የግብርና ዘርፍ ሆኗል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም አብዛሃኛዉ አካባቢዎችም ዉጤታማ የሆነ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት እየተመረተ ቢሆንም በክልሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ምርታማነቱ ከዚህ ግባ የሚባል አደለም፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ያነጋገራቸዉ አንዳንድ አርሶ አደሮች የአካባቢዉን የአየር ሁኔታ ያገናዘበ የስንዴ ዘር በምርምር ታግዞ ቢቀርብ በቂ ምርት ማምረት እንደሚቻል ገልጸው የክልሉ መንግስት ትኩረት እንድያደርግበት ጠይቀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ባበክር ሃሊፋ በበኩላቸው በአንዳንድ አካባቢዎች ለተፈጠረው የስንዴ ምርት መቀነስ የአርሶ አደሮች የግብዓት አጠቃቀም ችግር በዋናነት የሚቀመጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከምርጥ ዘር ጋር ተያይዞ የሚነሱ የአርሶ አደር ጥያቄዎችን ለመመለስም የተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችን ታሳቢ ያደረጉ እና የተሻለ ምርት ማስገኘት የሚችሉ አራት ዓይነት የምርጥ ዘር ግባዓቶች መዘጋጀታቸዉን ተናግረዋል፡፡
እንዚህን የምርጥ ዘር ግብዓቶችንም በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ነው የተናገሩት የቢሮ ሃላፊው፡፡
በዘመናይ የሻለም BGM










All reactions:
Melese Beyene and 20 others



All reactions:
Endris Ali, Damte Eteffa and 58 others

