NRDEP የአካባቢ ጥበቃና የመልሶ ማቋቋም ተግባር በተጨማሪ የጀመራቸው የልማት ስራዎች የሚበረታታ መሆኑን ተገለጸ፤
*************************************
ህዳር 9/2018 ዓ.ም አሶሳ፤
NRDEP የአካባቢ ጥበቃና የመልሶ ማቋቋም ተግባር በተጨማሪ የጀመራቸው የልማት ስራዎች የሚበረታታ መሆኑን የቤ/ጉ/ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ ተናግረዋል፤
የNRDEP ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ጥላሁን ከNRC ጋር በመተባበር ስደተኞችንና የአካባቢ ማህበረሰብ በአነስተኛ መስኖ ልማት እና በንብ እርባታ ስልጠና በመስጠት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፤
በተጨማሪም በስደተኞች የሚደርስ የአካባቢ ተፅዕኖ ለመቀነስ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና ለ2000 ቤተሰቦች የኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አቶ ጌታቸው ጥላሁን ገልጸዋል፤
የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በሆሞሻ ወረዳ ፆሬ አሩሜላና ሸርቆሌ ስደተኞች ካምፕ በመገኘት ለስደተኞች የተፈጠረ የስራ ዕድል አተገባበር ጎብኝተዋል፤

