የሌማት ትሩፋት ዋና ዓላማ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የአመጋገብ ሥርዓትን ማሻሻል ነው

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በሌማት ትሩፋት መርሐግብር ከሰባት ቢሊዮን ሊትር በላይ ወተት እና ከአራት ቢሊዮን በላይ የእንቁላል ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። 564 ሺህ ቶን ቀይ ሥጋና 127 ሺህ ቶን የዶሮ ሥጋ ምርት መገኘቱም ተመላክቷል።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዮሐንስ ግርማ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የቤተሰብ ብሎም በሀገር ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል፡፡
በዚህም በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ሊትር ወተት፣ 564 ሺህ ቶን ሥጋ፣ 127 ሺህ ቶን የዶሮ ሥጋ፣ 191 ሺህ ቶን ማር፣ 111 ሺህ ቶን ዓሣ እና አራት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን የእንቁላል ምርት ተገኝቷል ሲሉ ገልጸዋል።
እንደ ዶክተር ዮሐንስ ገለጻ፣ የሌማት ትሩፋት ዋና ዓላማ በሀገሪቱ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በቤተሰብ ብሎም በሀገር ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የአመጋገብ ሥርዓትን ማሻሻል ነው። በዚህም የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያ፣ ዘመናዊ የንብ ቀፎ፣ የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩት፣ የዓሳ ጫጩት እና ቴክኖሎጂዎችን…..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=126165
+2
All reactions:

33

All reactions:

Damte Eteffa, Benishangul Gumuz Education Bureau and 30 others